Listen

Description


ሰላም እንዴት ቆያችሁን ውድ የመሪ ፖድካስት ተከታታዮች:: በዛሬው ክፍላችን የመንግስት ተቋማት ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሆነውን እና በብዙ ለውጦች ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት CEO ይዘንላችሁ ቀርበናል። ሀና አርአያ ስላሴ ትባላለች: ሀና የኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት ድርጅት ከነበረበት የ የ 78 ሚሊየን ብር እዳ ወጥቶ በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ትርፍ እንዲያተርፍ የመሪነት ሚናን ተጫውታለች።በተጨማሪም ከአለም አቀፍ ፓስታ ቤቶች በሱ ደረጃ ከነበረበት 117 ደረጃ ወደ 68ኛ ከፍ እንዲል የበኩልዋን አበርክታለች : በህግ ትምህርት ከ አ.አ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪዋን የያዘች ሲሆን ከ University of New York ደግሞ በ legal theory ማስተርሷን ሰርታለች አንደ Mckensy & Company consulting firm , የጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ በአማካሪነት , በ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ኢንደስትሪያል ፓርክ ቪዥን ላይ ደግሞ ደፒውቲ ኮምሽነር አገልግላለች ። በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት ውስጥ በ CEO ነት እየሰራችም ትገኛለች።

ከአቅራቢዎቻችን ጋር በነበራት ቆይታ ስለ ፓስታ ቤት ጉዞዋ: የህይወት ልምዷን: ከባድ ነገሮችን የማድረግና የመቻል ምስጢር አጋርታናለች። የምትወዱት ቆይታ እንደሚሆን በማመን እንድትከታተሉት እንጋብዛለን ። መልካም ቆይታ !