Listen

Description


ሰላም እንዴት ቆያችሁን: የተወደዳችሁ መሪዎቻችን ዛሬ የ Web Sprix መስራችና CEO የሆኑትን ፡ ኢር . ዳዊት ብርሀኑን ይዘንላችሁ ቀርበናል ፡፡ ኢር. ዳዊት በአድስ አበባ ዩንቨርሲቲ በመምህርነት ያገለገሉ ሲሆን ፡ በግዜው ባገኙት የትምህርት እድል ምክንያትም ወደ ኔዘርላንድ በመጓዝ ፡ በኤሌክትሮኒክስ ማስተርሳቸውን ይዘዋል ፡ ከዛም በመቀጠል ፒኤችዲያቸውን ለመስራት ወደ አሜሪካን በተጓዙበት ፡ በአለማችን ትልቁ የሚባለውን የ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተቋም ሲስኮን በመቀላቀል ፡ እንደ መሪ ቴክኒካል ማርኬቲንግ ኢንጂነር ሰርተዋል ፡፡ ኢር. ዳዊት እሱን ትተው ከመጡ በዋላም ፡ በሀገራችን ከቴሌ ቀጥሎ የመጀመርያው የሆነውን ኢንተርኔት ሰርቪስ አቅራቢ ድርጅት ፡ ከምስረታ ጀምሮ አሁን ያለበት ደረጃ አድርሰውታል፡፡ እኛ ጋር በነበራቸው ቆይታም ፡ በሀገራችን ፡ አይፒ ቲቪ (cable TV) አገልግሎት ፡ እንዲሁም ማያ ስለተባለ ፡ ኢትዮጵያዊ ዩቱብ ፕላትፎርም ፡ በተጨማሪም ስለ ቢዝነስ አመራር ጥሩ ቆይታ አድርገናል ፡ ተጋበዙልን !