ጥያቄ፦ አንድ ሰው በስንት አመቱ ድርጅት ሊመሰርት ይችላል? 20፣30፣35? ሞሪስ ቻንግ የተባለው ሰው በ55 አመቱ ሰዎች ጡረታ በሚወጡበት ጊዜ እሱ ግን በማያውቀው ሃገር ባልተረጋጋ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የአለማችን 7ኛ ትልቁን ድርጅት መስርቷል። በዚህ ሳምንት ስለ ታይዋን ሰሚኮንዳክተር አምራች ድርጅት እናወራለን። የአለማችን 7ኛ ትልቁን ድርጅት ነው። አሁን ላይ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ልህቀት ላይ የሚገኝ እጅግ ግዙፍ ድርጅት ነው። በሁላችን እጅ፣ቤት፣ቢሮ፣ መኪና፣ እንዲሁም እጅግ በርካታ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ውስጥ የሚገኝ ፤ እጅግ አስደናቂ ስለሆነው ድርጅት እናወራለን። ስለ ጥንካሬው፣ ተጽእኖው እንዲሁም ምን ልንማር እንችላለን የሚለውን በሰፊው እንዳስሳለን። መልካም ቆይታ። እኛን ማግኘት ቢፈልጉ https://linktr.ee/kelemat