Look for any podcast host, guest or anyone
Showing episodes and shows of

Hana Haile

Shows

እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየአራት ልጆች እናት ፣ የተሸላሚ የልጆች መፅሀፍ ፀሐፊ ፣ የሳይበር ደህንነት ኢንጂነር ከዘኒት ከማል | Zinet Kemal children book authorበዚህ የእናትHood ፓድካስት ከዘኒት ከማል ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋ ፣ ስለ ፃፈቻቸው አራት መፅሀፎች ፣ ስለ ስራዋ ፣ ኑሮ በሚኒሶታ አሜሪካ ከአራት ልጆች ጋር ፣ ስለ ዘጠኝ አመት እስከ ማስተርስ የትምህርት ጉዞዋ ፣ ስለ ስኬት ሚስጥሯ ጨምሮ በስራዋ ስለተሸለመቻቸው ለመዘርዘር ከሚያዳግቱ ብዙ ሽልማቶቿ እና ሌሎችም በጣም ጠቃሚ ነገሮች ተነጋግረናል። እንደምትደሰቱበት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ። Zinet Kemal is a mother of four, a multi-award winning cybersecurity advocate and a four times best-selling author. She is currently working as Cloud Security Engineer at Best Buy and Board member at a non-profit, Black Girls in Cyber. She is a Georgia Tech University graduate with a Masters of Science degree in Cybersecurity. She earned a B.S. degree in Computer Science and LLB degree in Law. She wrote award-winning children's books, including "Proud in Her Hijab", "Oh, No ... Hacked Again!” and "See Yourself in Cybersecurity" promote empowerment, online safety and cyber careers for children. Zinet is a Tedx speaker, LinkedIn instructor, top 25 cybersecurity leader, also recognized as 2023 Minneapolis/St. Paul Business Journal 40 under 40. She has been featured in various media outlets including Good Morning America, 11Alive, BBC and CBS Minnesota - WCCO, ABC News, Yahoo News, AFROTECH and ebs. Website https://zinetkemal.com/ IG : https://www.instagram.com/zinet_kemal2024-06-271h 04እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየወላጅነት ጉዞ ከኦቲዝም ጋር ፤ የመልካም አባት ተምሳሌት ቢኒያም ንጉሴ #ethiopian #fatherlove #autism #enathoodበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከወትሮ በተለየ የአባቶችን ታሪክ ይዘን መጥተናል። የመልካም አባት ተምሳሌት የሆነው ቢንያም ንጉሴ የወላጅነት የአባትነት ጉዞውን ፥ እና የሶስተኛ ልጁን ታሪክ ፥ ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ የገጠመውን ውጣ ውረድ ፥ የተጠቀመበትን እና የረዳውን ሁሉ ነገር በሰፊው አጫውቶናል። ቢኒያም የሶስት ልጆች አባት ሲሆን ለልጆቹ በጣም ቅርብ እና በለት ተለት ኑሮአቸው ከፍተኛ ተሳትፎ የሚያደርግ አባት ነው። በተለይም ለሶስተኛ ልጁ በሚያደርገው በትጋት የተሞላ ክትተል የኦቲዝም ልዮ ፍላጎት ቢኖረው በጥሩ መሻሻሎችን እንዲያመጣ ሊረዳው ችሏል። 👉🏾 ቢኒያም ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@benyam77?_t=8nFob0z7gmE&_r=1 #habesha #ኢትዮጵያ #እናት #habeshatiktok #autismlife #autismawareness #ethiopian #fathersday2024-06-171h 03እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ለራሳችን እና ለልጆቻችን ከሳይበር ደህንነት ባለሙያ ከሁስኒ አወል ጋርበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ኢንጅነር እና አማካሪ ከሆነው ሁስኒ አወል ጋር የራሳችን እና የልጆቻችንን የሳይበር ደህንነት እንዴት እንደምንጠብቅ ተነጋግረናል። ጠቃሚ መረጃዎች እንደምታገኙበት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ። ሁስኒ አወል የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ኢንጅነር እና አማካሪ ነው። በአሁን ጊዜ ለToyota Financial Services በአማካሪነት እየሰራ ይገኛል። በኢትዮጵያ በግል እና የመንግስት የሳይበር ደህንነት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለማህበረሰባችን በሙያው አገልግሎት ይሰጣል። #amharic #ethiopia #ethiopian #cybersecurity #enat #enathood2024-05-3140 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodከAyla’s የልጆች መጫወቻ እና መማሪያ አዘጋጅ ሳራ ሱከር Ayla’s Kids Learning Tools with Sara Suker #የልጆች #ኢትዮጵያ #እናትበዚህ የእናትHood ፓድካስት ከሳራ ሱከር ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋና ለልጆች መጫወቻ እና መማሪያ ስለምታዘጋጃቸው ነገሮች ፣ ስለ ቢዝነስ እና ሌሎችም ነገሮች ተነጋግረናል። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። ሳራ የሁለት ልጆች እናት ናት። በቅርቡ የሙሉ ጊዜ ስራዋን በቤት ከልጆችዋ ጋር ለመሆን ወስና በቤት ቤተሰቧን እየተንከባከበች ትገኛለች። እንዲሁም ለልጆች መጫወቻ እና መማሪያ የሚሆኑ የተለያዮ በእጇ የምታዘጋጃቸውን ነገሮች ለገበያ ታቀርባለች። ስለገጠሟት ተግዳሮቶች ፣ ከእናትነት ልምዷ ፣ እና ሌሎችም ነገሮችን አካፍላናለች። መልካም ቆይታ!! Instagram : aylas_playthingz TikTok : Ayla's play thingz Phone no. 0966922080 Store location: Gurd shola, Holy City Center building, Ground floor G-08 #enathood #እናትhood #የልጆች #ኢትዮጵያ #እናት #habesha #ethiopian #amharic #smallbusinessowner2024-05-1440 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodከሆስፒታል ዉጪ ለመውለድ ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ፤ ለምን? ከህይወቴ ታደሰ ጋር (MPH)በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ ታደሰ ጋር ስለ ሶስተኛ ልጇ የወሊድ ዝግጅት ፣ ለምን ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ተጉዛ ከሚድዋይፍ ጋር ለመውለድ እንዳቀደች ፣ የእናትነት ጉዞዋን እና ለሎችም ተያያዥ ነገሮችን ተጨዋውተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት። ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። እንደ እቅድዋና ምኞትዋ ሶስተኛ ልጇን በ ማዋለጃ ማዕከል (Birthing Center) ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ወልዳለች። እንኳን ደስ አለሽ እያልን በተከታታይ ስላካፈለችው ልምድ እናመሰግናታለን። ህይወቴ በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ​⁠ ታካፍላለች። በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ሶስት ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት።2024-05-0848 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodወሊድ በአሜሪካ ከሆስፒታል ውጪ ፣ እናትነት ፣ ኑሮ በተለያየ አገር እና ጉዞ ከህይወቴ ታደሰ ጋር (ክፍል 1)በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ​⁠ ጋር ስለ ሶስተኛ እርግዝናዋ እንዴት ለወሊድ እየተዘጋጀች እንዳለች ፣ እናትነት ፣ በተለያዩ አገራትና ባህል ልጆችን ማሳደግ ፣ ወሊድ በሆስፒታል እና በማዋለጃ ማዕከል (birthing center) እና የመሳሰሉትን ነገሮች ተጨዋውተናል። መልካም ቆይታ። ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ታካፍላለች። ህይወቴ በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት። #ethiopian #habesha #amharic #ኢትዮጵያ #birth #childbirth #pregnancy2024-05-0151 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodኦቲዝምና ተመሳሳይ ኑሮሎጂክ መዛባትን የሚረዳ አመጋገብ / A diet that helps with Autism and related disorderOur latest podcast opens the world of autism motherhood, where challenges meet triumphs, especially when raising a child with autism. Let’s discover together Sel Seyoum’s book on how a healing diet program tailored for autism can be a game-changer, offering crucial support and day to day management. From modern cities to remote corners of countries, families with children in the spectrum and related disorders find help and guidance in this dedicated book on nutrition, navigating the unique path of autism with strength and resilience. Buy “Autism Lifestyle” handbook on Amazon 👉🏽 https://a.co/d/f3roRxl 👉🏽 Sel’s Instagram : [https://www...2024-04-241h 10እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየጥቁር እናት ነኝ ፀሀፊ እና ገጣሚ መሰረት ክንፈ ጋር የተደረገ ቆይታ - ስለ ኦቲዝም #autismawareness #enathoodበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከመሰረት ክንፈ ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋ ፥ ልዮ ፍላጎት ያለውን ልጅዋን ስታሳድግ የሚገጥማትን የለት ተለት ኑሮ ፥ ስለመፅሀፏ “የጥቁር እናት ነኝ” ፥ ስለምትሰራው የበጎ አድራጎት ስራ እና ሌሎችም ተጨዋውተናል። መሰረት ክንፈ “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሀፍ ፀሀፊ እና ገጣሚ ስትሆን የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናት። የመጀመሪያ ልጇ ኦትስቲክ ወይም ልዮ ፍላጎት ያለሁ በመሆኑ የገጠማትን ውጣ ውረድ ፥ የህይወት እይታዋን እና ትዝታዎችዋን በግጥም አስውባ በማቅረብ ትታወቃለች። “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሃፍ ሽያጭ ለበጎ አድራጎት በማዋል በኢትዮጵያ የሚገኙ የተቸረጉ እናቶችና ልጆችን እየረዳች ለብዙዎች መትረፍ ችላለች። መልካም ቆይታ። “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሀፍ Amazon ላይ ይገኛል። 👉🏽 https://a.co/d/13Pp8Ys #ethiopia #amharic #ethiopian #autism #እናት #ኢትዮጵያ #habesha2024-04-091h 29እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodስለ ኦቲዝም ከሊያ ስዮም ከ Reaching Families ኘሬዝዳንት ጋር / Autism with Leah Seyumበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሊያ ስዩም የ Reaching Families Advocacy and Support Group መስራችና ኘሬዝዳንት ጋር ስለ ኦቲዝም (ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች) ሰፋ ያለ ውይይት አድርገናል። ሊያ የግል የእናትነት ጉዞዋን እንዲሁም እየመራች ያለችው የበጎ አድራጎት ድርጅት ዉስጥ የሚሰሩ ስራዎች እና ማህበረሰባችን ስለ ኦቲዝም ማወቅ ያለበትን ሁሉ ከሙያ ልምዷ ጨምራ አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። ✨ሊያ ስዩም የአራት ልጆች እናት ስትሆን ሁለቱ ልጆችዋ ኦትስቲክ ወይም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ናቸው። በዚህም የተነሳ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆችን እና ወላጆችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስርታ ዳላስ ቴክሳስን ጨምሮ በሌሎች ትላልቅ የአሜሪካ ግዛት ከተሞች ያሉ ኢትዮጵያን እና ኤርትራውያን ወገኖች በመደገፍ እና ድርጅቱን በኘሬዝዳንትነት በማገልገል ላይ ትገኛለች። #autismawareness #enathood Reaching Families Advocacy and Support Group Website 👉🏾 https://reachfamilies.org/ Facebook 👉🏾 https://www.facebook.com/groups/454918007982318/ YouTube 👉🏾 https://youtube.com/channel/UCPOeeQv6d9qvXNJ2Gl0_94Q2024-04-021h 21እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodስለ GAPS አመጋገብ እና በቤት ውስጥ ልጆችን ትምህርት ማስተማር ከሜላት ማሞ ጋር (MPH) ክፍል 2 - Gut & Psychology Syndromeበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ካለፈው የቀጠለ ዉይይት ከሜላት ማሞ ጋር ስለ GAPS አመጋገብና ልጆችን በቤት ውስጥ ስለማስተማር ተጨዋውተናል። ሜላት በተከታታይ ሁለት ክፍሎች የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። ሐሳብና አስተያየታችሁን ላኩልን። መልካም ቆይታ!! ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት። በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰብዋን በመንከባከብ ላይ ትገኛለች። ማሳሰቢያ:- ይህ መረጃ የግል ልምድ እንደማስተማሪያ እንዲሆን የቀረበ ነው። የህክምና ምክር አይደለም። ለግል ጤና የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!!2024-03-1731 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodስለ GAPS አመጋገብ ፣ እናትነት እና ኑሮ በአቡዳቢ ከሜላት ማሞ (MPH, licensed ASCP)በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሜላት ማሞ ጋር ስለ እናትነት ፣ በቤት ውስጥ ሙሉ ጊዜ መሆንና ቤተሰብን መንከባከብ ፣ እና ስለ ኑሮ በአቡዳቢ ተጨዋውተናል። በሰፊው የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (**Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች።** ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ!! ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት። በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰብዋን በመንከባከብ ላይ ትገኛለች። ማሳሰቢያ:- ይህ መረጃ የግል ልምድ እንደማስተማሪያ እንዲሆን የቀረበ ነው። የህክምና ምክር አይደለም። ለግል ጤና የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!!2024-02-201h 08እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየቆዳ ውበት አጠባበቅ ፣ እራስን መንከባከብ እና እናትነት ከHanSim Skin ባለቤት ምልጃዬ ስሜ ጋር Skincare, Self-care, & Motherhoodበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከምልጃዬ ስሜ የሃንሲም የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች - HanSim Skin መስራች እና ባለቤት ጋር የፊትና የሰውነታችን ቆዳ እንዴት መንከባከብ እንደምንችል ተወያይተናል። በተጨማሪም እራስን መጠበቅ እና እናትነት እንዴት አብሮ ማስኬድ ይቻላል የሚሉ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል። የቢዝነስ ስራዎችዋን ከቤተሰብ ሃላፊነት ጋር እንዴት እንደምታስኬድ የግል ልምዷን ጨምራ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። የ HanSim ምርቶችን ለማግኘት:- HanSim Online Store 👉🏾 https://hansimskin.com/ በአዲስ አበባ የሚገኙ መሸጫና አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ:- 1. የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች መሸጫ :- ሌበኔዝ ህንፃ Lebenze Tower ጋዜቦ አደባባይ 1ኛ ፎቅ 2. Hansim Salon and Spa ሙሉ የፀጉር የውበት ሳሎን እና የቆዳ እንክብካቤ አገልግሎት :- ሆሊ ሲቲ ሴንተር Holy City Center 2ኛ ፎቅ ጉርድ ሾላ በስልክ ቁጥር 0931888855 ይደውሉ።2023-12-071h 01እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodፍጹም ተፈጥሮአዊ ወሊድ በዉሃ ውስጥ ፤ የሶስተኛ ልጃችን የወሊድ ታሪክ - Super Natural Water Birthየዚህ ክፍል የእናትHood ፓድካስት ስለ ሶስተኛ ልጄ የወሊድ ታሪክ የተመለከተ ነው። የወለድኩት በወሊድ ማእከል/birthing center ውስጥ ያለ ምንም መድሀኒት ፣ ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ከሚድዋይፎች እገዛ ጋር ነበር። ለሁለተኛ ጊዜ ሰላም የሰፈነበት ወሊድ በዉሀ ዉስጥ ተሳክቶልኛል። ቪዲዮን መመልከት ከፈለጋችሁ በYouTube ታገኙታላችሁ።2023-11-1512 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየወሊድን ምጥ በኢፒዱራል አንስቴዚያ ወይስ ያለ ኢፒዱራል አንስቴዚያ Childbirth with Epidural Anesthesia vs withoutበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የወሊድ ምጥ በኢፒዱራል አንስቴዚያ (Epidural Anesthesia) ወይስ ያለ ኢፒዱራል አንስቴዚያ በሚል በሁለቱም መንገድ ያለኝ ልምድ አካፍያለሁ። የመጀመሪያ ልጄን በኢፒዱራል አንስቴዚያ ስወልድ ያጋጠመኝን ፤ ሁለተኛ ልጄን ያለምንም መድሀኒት ስወልድ የነበረውን ሁኔታ በንፅፅር እና ሶስተኛ ለመውለድ እንዴት እየተዘጋጀሁ እንደሆነ ጨምሮ ተያያዝ ነገሮችን አንስቻለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ። መልካም ጊዜ!! 👉🏾  Everything You Need to Know about Epidural Anesthesia with Dr. Betelehem M. Asnake, MD – ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ ዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ 👉🏾  The Mama Natural Week-by-Week Guide to Pregnancy and Childbirth 👉🏾  Christian Hypo Birthing2023-09-3016 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ ከዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ ጋር - Everything You Need to Know about Epidural Anesthesiaበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል አንስቲዚኦሎጂስት ከሆነችው ዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ ጋር ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ/Epidural Anesthesia ማለትም በአብዛኛው ጊዜ በወሊድ እና በቀዶ ጥገና ጊዜ ስለሚሰጠው የማደንዘዣ መድሀኒት ተወያይተናል። ሙያዊ ልምዷን ጨምራ በኢፒዶራል አንስቴዚያ ዙሪያ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ መልስና ማብራሪያ ሰጥታናለች። መልካም ቆይታ። Dr. Betelehem M. Asnake, MD is a board certified Anesthesiologist and anesthesia global health director at the University of California Los Angeles. 👉🏾 Dr. Betelehem M. Asnake, MD - https://www.uclahealth.org/providers/betelehem-asnake She is  also a founder and manager of Mulu Mentor, which helps underrepresented and disadvantaged pre-medical students navigate the medical school application process through targeted mentorship. 👉🏾 Mulu Mentor - https://www.mulumentor.com/2023-09-151h 09እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodበእርግዝና ጊዜ ማጥባት እና ሁለት ልጆችን በጋራ ማጥባት - Breastfeeding during Pregnancy and Tandem Nursingበሶስት አመት የጡት ማጥባት ጉዞዬ ውስጥ ያደረግኩት በእርግዝና ጊዜ ማጥባት እና ሁለት ልጆችን በጋራ ማጥባት ብዙ ጥያቄና አስተያየት ያስተናገድኩበት ነው። ሳይንስ የሚለውን እና የራሴን ልምድ በዚህ ክፍል አካፍያለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ። 💫 ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት። 🌟 የቀደሙ የጡት ማጥባት ዉይይቶች 👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለልጆች https://youtu.be/WodjPq3RHJE?si=Pw9CGJajEzNrfeCs 👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለእናቶች https://youtu.be/TVHwglULAD4?si=oKG_ePx44sxwLHQb 👉🏾 የእናት ጡት ወተት ማለብ ጠቃሚ ልምዶች https://youtu.be/YXb-DU9u2hM2023-09-0228 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየእናት ጡት ወተት ማለብ ጠቃሚ ልምዶች ከብርቱካን አሊ (CRNA, DNP) - Breast Milk Pumping Best Practiceየነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በተከታታይ የጡት ማጥባት ዉይይቶችን እያደረግን በመሆኑ ከአድማጮች የተነሱ ስለ ጡት ወተት ማለብ እና አቆይቶ መጠቀም ጥያቄዎችን ከብርቱካን አሊ ጋር በመወያየት ከልምድና ከሙያዋ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ብርቱካን የሶስት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ Certified Registered Nurse Anesthetist, (CRNA DNP) ማለትም ነርስ እና የማደንዘዣ ወይም የሰመመን መድሀኒት ሰጪ ናት። 🌟 በውይይታችን የተጠቀሱ ጡት ወተት ማለቢያ እና ማስቀመጫ - Medela Breast Pump / የጡት ወተት ማለቢያ https://www.medela.us/breastfeeding/products/breast-pumps - Spectra Breast Pump / የጡት ወተት ማለቢያ - [https://www.spectrababyusa.com](https://www.spectrababyusa.com/) - Elvie Hand Free Portable Breast Pump / ተንቀሳቃሽ የጡት ወተት ማለቢያ - https://www.elvie.com/en-us/shop/elvie-pump - WillowHand Free Portable Breast Pump / ተንቀሳቃሽ የጡት ወተት ማለቢያ - [https://onewillow.com](https://onewillow.com/) - Mason Jar 4 oz / ጠርሙስ ለወተት ማስቀመጫ - https://amzn.to/47RdDZG - Mason Jar 8 oz / ጠርሙስ ለወተት ማስቀመጫ - https://amzn.to/47RdDZG - Pack It Ice Bag / የበረዶ ቦርሳ - https://amzn.to/3KXtJXE - Breast Milk Warmer / የጡት ወተት ማሞቂያ - https://amzn.to/3Ebcfn02023-08-271h 00እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየእናት ጡት ወተት ጥቅም ለልጆች ከህይወቴ በቀለ (MPH) - Benefits of Breast Milk for Childrenየነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ የእናት ጡት ወተት ለልጆች ያለውን ጥቅም ተወያይተናል። እናም ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። በተጨማሪም በህይወቴ የYouTube channel ላይ ጡት ማጥባት ለእናቶች ያለውን ጥቅም። ተወያይተናል። በጣም ጥሩ መረጃዎችን የያዘ ነው። እንደተመለከቱት እጋብዛችሁአለሁ። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። 💫ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት።2023-08-131h 16እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየእናቶች ታሪክ በአለም ዙሪያ - ረቂቅ አዕምሮ ከዳላስ (Mother's Stories Around the World)በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ረቂቅ አዕምሮ የእናትነት ጉዞዋ አካፍላናለች። እናትነት ለሷ ምን ማለት እንደሆነ ፣ የዕለት ተለት ስኬትና ተግዳሮቶችን ጨምሮ እና ኑሮ በዳላስ ቴክሳስ ምን እንደሚመስል አጫውታናለች። መልካም ቆይታ። ረቂቅ አዕምሮ የአንድ ቆንጆ ሴት ልጅ እናት ናት። ከባለቤቷ እና ከልጇ ጋር በቴክሳስ ዳላስ ትኖራለች። ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጇን እና ቤተሰቧን ትንከባከባለች።2023-07-291h 21እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየቤት ዉስጥ ት/ት፣ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪነት እና ከስክሪን ነጻ የሆኑ ልጆች - Homeschooling, Bilingualism, and Screen free kidsበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከቤተልሔም ፀጋዬ ጋር በቤት ውስጥ ልጆችን በሙሉ ሰዓት ማስተማር ፣ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ መሆን እና ልጆችን ከስክሪን (ከቲቪ እና ከስልክ) ነፃ አድርጎ ስለማሳደግ ተነጋግረናል። ቤተልሔም ብዙ ጠቃሚና አነቃቂ መረጃዎችን ከወላጅነት ልምዷ ጨምራ አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። ቤተልሔም የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ልጆችዋን በሙሉ ጊዜ በቤትዋ ት/ቤት ሳትልክ ታስተምራለች። ልጆችዋ አማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከዛም ጋር በተገናኘ የአማርኛ ቋንቋ ማስተማርያ የርቀት (በዙም) የምታስተምርበት ፋኖስ የሚባል ማስተማርያ አላት። በተጨማሪም ቤተልሔም የልጆች መማርያ መፅሀፍትንም ታዘጋጃለች። ከፋኖስ ድህረ ገፅ እነዚህን የአማርኛ መማርያ መፅሀፋትና ሌሎች መርጃ መሳሪያዎች ታገኛላችሁ። ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ። 👉🏾 https://www.myfanos.com/2023-07-141h 03እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየሚድዋይፈሪ (Midwifery) አገልግሎት በኢትዮጵያ ከረድኤት እንዳለው (Clinical midwife, Msc) -Midwifery care in Ethiopiaበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከረድኤት እንዳለው ጋር ስለ ሚድዋይፈሪ (Midwifery) አገልግሎት ተወያይተናል። ለሴቶች እና እናቶች የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲሁም በእርግዝና እና ወሊድ ጊዜ የሚድዋይፍ (Midwife) የሚሰጡትን እገዛ ጨምሮ ሌሎችም መረጃዎች አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። ረድኤት እንዳለው በኢትዮጵያ የምትኖር ሚድዋይፍ (Clinical midwife, Msc) ናት። በአቻሞ ዩንቨርስቲ አስተማሪ ናት። እማ ዛሬ (Ema Zaire) በሚባል የYoutube channel ስለእናቶች እና የልጆች ጤና ጠቃሚ መረጃዎችን ታካፍላለች። እዚህ ጋር ልታገኙት ትችላላችሁ 👉🏾 https://youtube.com/@emazare63152023-06-2342 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodጤናማ ኑሮ እና ከመርዛማ ንጥረ ነገር የፀዳ የአኗኗር ዘይቤ ከህይወቴ በቀለ (MPH) - Healthy & non toxic livingበዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ ጤናማ ኑሮ እና ከመርዛማ ንጥረ ነገር የፀዳ የአኗኗር ዘይቤ ተወያይተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ወይም ለቤተሰብ አካፍሉት።2023-06-131h 16እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodየእናቶች የአዕምሮ ጤና ከሊዲያ ዱሜሳ (Ph.D.) ጋር የተደረገ ዉይይት - Maternal Mental Healthከክሊኒካል ሳይኮሎጆስት ሊዲያ ዱሜሳ (Ph.D.) ጋር ስለ እናቶች የአዕምሮ ጤና ተወያይተናል። ከእርግዝና እስከ አንድ አመት ድህረ ወሊድ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮች እና ምልክቶቻቸው ፣ እርዳታ እንዴት ማግኘት እንደምንችል እናም የማህበረሰብ ድጋፍ ጥቅምን ጨምሮ ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮች ተነጋግረናል። መልካም ቆይታ። 👉🏾 ከሊዲያ ዱሜሳ (Ph.D.) አገልግሎት (therapy) ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ በመጠቀም ስልክ ፣ ኢሜል እና አድራሻ ያግኙ። https://www.psychologytoday.com/us/therapists/lediya-dumessa-washington-dc/7964622023-06-0144 minእናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodልጆች ተኮር አመጋገብ (Baby - Led Weaning) ከጊፍቲ ባዮ ጋር የተደረገ ቆይታበዛሬው የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከጊፍቲ ባዮ ጋር ቆይታ ይኖረናል። ዉይይታችን የህፃናት ልጆች አመጋገብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ህፃናት ልጆች በተለይም ከስድስት ወር በኃላ ተጨማሪ ምግብ እንዴት እናስጀምራለን? ምን አይነት የአመጋገብ ዘዴዎች አሉ? ፣ እንዲሁም እንዴት ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ እንችላለን? እና ህፃናት እራሳቸውን መመገብ እንዲችሉ እንዴት መርዳት እንምንችል ጨምሮ ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን እናነሳለን።2023-05-231h 06እናትHood | EnatHoodእናትHood | EnatHoodእናትHood ፖድካስት - እንኳን ደህና መጣችሁ!! Welcome to EnatHood!!እናትHood ፖድካስት ስለ እናትነትና እና እናት ስለሚመለከታት ሁሉ ነገር ላይ ትኩረት የሰጠ ፖድካስት ነው። እርግዝና ፣ ወሊድ ፣ የልጅ እንክብካቤ ፣ ወላጅነት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናል። ተዘጋጅቶ የሚቀርበው በሐና ኃይሌ ከ enathood.com ጦማር ነው። EnatHood is a podcast dedicated to motherhood and what a mother cares for. It covers a range of topics, including pregnancy, childbirth, baby care, parenting, and healthy lifestyle choices. It is brought to you by Hana Haile from enathood.com.2023-05-0503 min