podcast
details
.com
Print
Share
Look for any podcast host, guest or anyone
Search
Showing episodes and shows of
Yetena Weg ®
Shows
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የህክምና መረጃ ሚስጥራዊነት, ፈቃድ አሰጣጥና የሀኪም ታካሚ ግንኙነት/Confidentiality, Consent and Patient-Physician Relation
በዶ/ር ብሩክ አለማየሁ እና ሃይማኖት ግርማ በተዘጋጀው በዚህ ፖድካስት ዶ/ር አስቻለው ወርቁ ስለ ህክምና ስነምግባር በተለይም የህክምና መረጃ ሚስጥራዊነት፣ ፈቃድ አሰጣጥና የሀኪም ታካሚ ግንኙነት ላይ ሰፊ አስተማሪ ማብራርያ የሰጡ ሲሆን ከዚህ አንፃር በሀገራችን ከዚህ አኳያ መሻሻል ስላለባቸው ክፍተቶችና አካሄዶች ተወያይተናል። In this podcast hosted by Dr. Brook Alemayehu and Haymanot Girma, Dr. Aschalew worku discusses aspects of medical Ethics particularly Confidentiality, Consent and Patient-Physician and the situation in our country. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-07-31
2h 06
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ሞትና መሪር ሀዘን/ Grief and Loss
በዚህ ፖድካስት በዶ/ር ሄርሞን አማረ አስተናባሪነት ከእንግዶቻችን ሄኖክ ኃይሉ እና ሞገስ ገ/ማርያም ስለ ሞት፣ ሀዘን፣ የተራዘመ ሀዘን፣ እና የመቋቋሚያ ዘዴዎች ተወያይተናል። In this podcast moderated by Dr. Hermon Amare, our guests Henock Hailu and Moges G/mariam discussed about the impact of losing a loved one, the stages of griefing, about prolonged grief and coping mechanisms. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-07-24
1h 45
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የአካል ጉዳተኝነት እና የህክምና ትምህርት ተደራሽነት/ተካታችነት በኢትዮጵያ- Accessibility, Inclusiveness and Disability Rights in Ethiopian Medical Schools
በዚህ ፖድካስት አካል ጉዳተኞች በትምህርት ሥርዓቱ በተለይም በህክምና ትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን የመዋቅር እና የአመለካከት ችግሮች በሚመለከት ከእንግዶቻችን ፕሮፌሰር አበበ በቀለ እና አቶ ዳኛቸው ዋኬን ጋር አስደናቂ ውይይት አድርገናል። In this podcast, we had a fascinating discussion with our guests Professor Abebe Bekele and Ato Dagnachew B. Wakene concerning the structural and attitudinal obstacles that people with disability face in the educational system and in particular in our medical schools. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-07-17
2h 18
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የጤና ወጪና እና የጤና መድህን በኢትዮጵያ/ Health care financing and Health Insurance in Ethiopia
በዚህ ፖድካስት ስለ ጤና መድህን አስፈላጊነት እና በሀገሪቱ የጤና መድህን ስርዓትን ለማቋቋም ስለሚደረገው ጥረት ተወያይተናል። እንግዶቻችን ፍሬህይወት አበበ፣ አለማየሁ ካብተይመር፣ ህሊና ከበረ እና ዶ/ር ቅድስት መላኩ ነበሩ። In this podcast, we discussed about the need of health insurance and the efforts to institute health insurance systems in the country. Our guests were Frehiwot Abebe, Alemayehu Kabtyimer, Helina Kebere and Dr. Kidist Melaku. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-07-01
2h 04
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
በሕግና በአዕምሮ ሕመም መካከል ያለው መስተጋብር/ The Intersection between Mental Health and the law
በዚህ ፖድካስት በሕግና በአዕምሮ ሕመም መካከል ስላለው መስተጋብር በኢትዮጵያ ብቸኛ ፎሬንዚክ ሳይኪያትሪስት ከሆነው ከዶ/ር አስናቀ ልመንህ ጋር ተወያይተናል። In this podcast, we discussed about the interaction between law and mental illness with the one and only Forensic Psychiatrist in Ethiopia, Dr. Asnake Limenih. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-06-26
2h 22
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የህክምና ትምህርት ጥራት በኢትዮጵያ/ Quality of Medical Education in Ethiopia
In this podcast, we discussed about the state of Medical Education in our country. We were joined by 1. Assegid Samuel, FMOH, (Director, Human Resources for Health Development Directorate) 2. Abiy Debay, HERQA/ETA (Director for Accreditation) 3. Dr. Elilta Nega, FMOH, (Officer, Human Resources for Health Development Directorate) 4. Sabrina Zeleke (Medical Student, EMSA) 5. Dr. Tsedeke Asaminew (Consultant Ophthalmologist, Vitreoretinal subspecialist, Medical Educator) በዚህ ፖድካስት ውስጥ በአገራችን ስላለው የሕክምና ትምህርት ሁኔታ ተወያይተናል። እንግዶቻችን 1. አሰግድ ሳሙኤል ጤና ሚኒስትር (የሰው ሃይል ለጤና የልማት ዳይሬክቶሬት) 2. አቢይ ደባይ ኢ.ት.ስ.ባ (የእውቅና ዳይሬክተር) 3. ዶ/ር እልልታ ነጋ፣ ጤና ሚኒስትር (የሰው ሃይል ለጤና የልማት ዳይሬክቶሬት) 4. ሳብሪና ዘለቀ (የህክምና ተማሪዎች ማህበር) 5. ዶ/ር ፀደቀ አሳምነው (የአይን ሐኪም ስፔሻሊስት፣ የቫትሮ-ሬቲናል ንዑስ ስፔሻሊስት፣ የህክምና አስተማሪ) --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-06-04
2h 13
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የአንቲባዮቲክ (ፀረ ተውኃሲያን መድኃኒቶች) ሽያጭ ደንብና ቁጥጥር በኢትዮጵያ/ Regulation of Antibiotic Sale in Ethiopia
በዚህ ፖድካስት ውስጥ፣ ስለ ተቆጣጣሪው አካል አወቃቀር፣ ስለ አጠቃላይ የቁጥጥር ተግባራት፣ ስላሉት ተግዳሮቶችና መፍተሄዎቹ ተወያይተናል። እንግዶቻችን አስናቀች አለሙ (ኢ.ም.መ.ቁ.ባ)፣ ጌታቸው አለምከረ (አ.አ.ዩ የፋርማሲ ትምህርት ቤት)፣ ዶ/ር እስከዳር ፈርዱ (አ.አ.ዩ.፣ ተላላፊ በሽታ ክፍል) እና ሚሊዮን ትርፌ (ኢ.ም.መ.ቁ.ባ) ነበሩ። In this podcast, we discussed about the structure of the EFDA, the overall regulatory activities including the challenged and the way forward. Our guests were Asnakech Alemu (EFDA), Getachew Alemkere (AAU School of Pharmacy) , Dr. Eskedar Ferdu (AAU, Infectious Disease Unit) and Million Tirfe (EFDA). ኢ.ም.መ.ቁ.ባ/EFDA: የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን/ Ethiopian Food and Drug Authority --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-05-21
1h 52
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ሲጋራ እና ሺሻ/ Smoking Cigarettes and Hookah
በዚህ ፖድካስት ስለ ሲጋራ እና ሺሻ የጤና ተጽእኖ ከእንግዶቻችን ዶ/ር ኤርሚያስ ካቻ (ፐልሞኖሎጂስት እና ክሪቲካል ኬር ስፔሻሊስት) እና ዶ/ር ዮናስ ላቀው (ሳይካትሪስት) ጋር ተወያይተናል። In this podcast, we discussed about the health impacts of Cigarette and Hookah with our guests Dr. Ermias Kacha (Pulmonologist and Critical Care Specialist) and Dr. Yonas Lakew (Consultant Psychiatrist) --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-05-15
1h 46
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የወሳኝ መድሀኒቶች አቅርቦት በኢትዮጵያ/ Access to Essential Medicine in Ethiopia
በዚህ ፖድካስት ስለ ወቅታዊው የመድሃኒት አቅርቦት ሁኔታ ተነጋግረናል። በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ ዘላቂ አቅርቦትን የሚያደናቅፉ ተግዳሮቶችን እና መፍትሄዎችን እናነሳለን። እንግዶቻችን ዶ/ር ሎኮ አብርሀም (የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ባለስልጣን የቀድሞ ዳይሬክተር) አማኑኤል ዝናረ (የግል ዘርፍ) እና ሰለሞን አብደላ (ጤና ሚኒስትር) ናቸው። In this podcast, we discuss about the current state of medication supply in the country. We also raise the challenges that are currently hampering sustainable supply and the possible solutions. Our guests are Dr. Loko Abraham (former Director of EPSA), Amanuel Zinare (Private Sector) and Solomon Abdela (FMOH/PMED). --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-05-01
2h 20
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የስኳር በሽታ እና ከልክ ያለፈ ውፍረት/ Diabetes and Obesity
በዚህ ፖድካስት ስለ ስኳር በሽታ አጋላጮች፣ ምልክቶቹ እና ስለ ሕክምናው ከእንግዶቻችን ከዶ/ር ቃልኪዳን አላቸው (የስኳርና የኢንዶክራይን ህመሞች ስፔሻሊስት) እና ከትርሲት ደምሰው (የስነ ምግብ ባለሙያ) ጋር ተወያይተናል። In this podcast, we discuss about diabetes, risk factors, clinical presentation and medical care with our guests Dr. Kalkidan Alachew (Endocrinologist) and Tirsit Demissew (Dietician). --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-04-18
2h 08
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የጤና መረጃ ጥራት በኢትዮጵያ/ Quality of Health Data in Ethiopia
በዚህ ፖድካስት የጤና መረጃ በጤና ስርዓታችን ውስጥ ስላለው ጠቀሜታ፣0 ያሉትን ተግዳሮቶች፣ እድሎችን እና ወቅታዊ ጥረቶችን እናነሳለን። ተወያዮቻችን ናኦድ ወንድይራድ፣ ዶ/ር ደሳለኝ በቀለ፣ ሰናይት ቢተው እና ዶ/ር የቆየሰው ወርቁ ናቸው። In this podcast, we discuss about the importance of health data in our health system and raise the challenges, opportunities and current efforts. Our panelists are Naod Wondirad, Dr. Desalegn Bekele, Senait Bitew and Dr. Yekoyesew Worku --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-04-09
2h 27
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ከድባቴ ጋር መኖር/ Living with Depression
በዚህ ፖድካስት ከያፌት ከፈለኝ፣ ከዶ/ር የፍሬዘር ገዛኸኝ፣ ከዶ/ር ማጂ ኃ/ማርያም እና ከዶ/ር ሄርሞን አማረ ጋር ስለ ድባቴ፣ የመቋቋሚያ ክህሎቶች እና የህክምና አገልግሎት እንወያያለን። In this podcast, we discuss about Depression, coping skills and medical care with Yafet Kefelegn, Dr. Yefrezer Gezahegn, Dr. Maji H/Mariam and Dr. Hermon Amare. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-04-03
2h 00
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የኩላሊት ህክምና በኢትዮጲያ ምን ይመስላል? Kidney disease care, Dialysis and Kidney transplant service in Ethiopia
በዚህ ፖድካስታችን የኩላሊት ህመም ስፔሺያሊስት ከሆኑት ዶ/ር ቤዛዬ አበበ ፣ ዶ/ር ሰይፈሚካኤል ጌታቸው እና ዶ/ር ፍፁም ጥላሁን ጋር ስለ ኩላሊት ጤና አጠባበቅ፣ ስለ ኩላሊት መድከም፣ ስለ ዳያሊሲስ እና የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ውይይት አድርገናል። In this podcast, we discussed kidney health, kidney failure, dialysis and kidney transplantation services in Ethiopia with our guest nephrologists Dr. Bezaye Abebe, Dr. Seyfemichael Getachew and Dr. Fitsum Tilahun. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-03-28
2h 17
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የጤና ባለሙያዎቻችን መታከት፣ ለምን?/ Burnout among our Healthcare Professionals
በዚህ ፖድካስት ስለ የጤና ባለሙያዎቻችን መታከት ከዶክተር መድህን ሰላሙ ጋር ተወያይተናል። ዶ/ር መድህን በዚህ ርዕስ ላይ ሰፊ ጥናት አድርገዋል። የጤና ሚኒስቴር ኃላፊዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አቅርበናል። In this podcast, we discussed about burnout among our health care professionals with Dr.Medhin Selamu on our Yetena Weg Club House session. Dr.Medhin has done an extensive research on this topic . We also featured officials from the Minstry of Health and other stakeholders. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-03-28
2h 15
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የስትሮክ ህመም ምንድነው? ህክምናውስ? ከዶ/ር መሀሪ ጋር / Stroke - Types, Diagnosis and management with Dr.Mehari
ስለ ስትሮክ ህመም ፣ ምርመራ እና ህክምና በጤና ወግ ክለብ ሀውስ ከዶ/ር መሀሪ ገብረየኋንስ ጋር ያደረግነውን ውይይት ነው። ሰለ ስትሮክ ህመም አይነቶች፣ በምን ምክንያት እንደሚከሰት ፣እንዴት እንደሚታከም እና እንዴት መከላከል እንደምንችል ተወያይተናል። ዶ/ር መሀሪ በ University of Texas South Western የ ኒውሮሎጂ እና ስትሮክ ሰብ ስፔሺያሊስት ናቸው። በሀገራችንም ኢትዮጲይ ያሉ ባለሙያዎች በውይይቱ ተካፋይ ነበሩ። በሀገራችን ያለውን የስትሮክ ህክምና ደረጃ ያስረዱናል። This is the conversation with Dr. Mehari Gebreywanes, we talked about definition of stroke, its diagnosis and treatment. We also discussed the types of stroke, and how to prevent it. Dr. Mehari is a neurology and stroke specialist at the University of Texas Southwestern. Experts from our country, Ethiopia, participated in the discussion. They explain the level of stroke treatment in our country. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-03-27
1h 58
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
በጦርነት ወቅት ስለሚፈጠሩ የአእምሮ ጤና ችግሮች / The Impact of War/Conflict on Mental Health, focus in Ethiopia
ከጦርነትና ግጭቶች ጋር ተያይዞ ስለሚፈጠሩ የአእምሮ ጤና ችግሮችና ችግሩን ለመፍታት በኢትዮጵያ ምን እንደታሰበ ከአእምሮ ጤና ባለሞያ እና ከጤና ሚኒስቴር ሀላፊዎች ጋር የተደረገ ውይይት A discussion with mental health experts and Ministry of Health officials about mental health problems that arise in connection with war and conflict and what is being planned in Ethiopia to solve the problem --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2022-02-03
1h 52
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ስለ ጨጓራ በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች። ቆይታ ከ ዶ/ር ኤርምያስ ጋር።
የጨጓራ ህመም አይነቶች ምንድናቸው ? ምን ያህል ሰው በዚህ ህመም ያያዛል? ለበሽታው የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምንድናቸው? የህመም ምልክቶቹ ምንድናቸው? ምርመራው ምን ይመስላል? ህክምናውስ ምን ይመስላል? በራሳችን ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ምን ይመስላሉ? እነዚህን እና ሌሎች ጠቃሚ ጥያቄዎች ላይ እንወያያለን። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2021-08-11
34 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
What you should know about Rheumatoid arthritis ? የ ሪህማቶይድ የ መገጣጠሚያ ህመም ምንድነው?
What you should know about Rheumatoid arthritis ? የ ሪህማቶይድ የ መገጣጠሚያ ህመም ምንድነው? ለህመሙ የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምንድናቸው ? ምልክቶቹ ምንድናቸው ? ምርመራዎቹ ምንድናቸው ? ሕክምናው ምን ይመስላል ? በዚህ ፖድካስት በዝርዝር እንወያያለን --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2021-06-05
25 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Updates on COVID-19 Infection and Vaccinations. የ ኮቪድ 19 በሽታ እና ክትባቶቹ ላይ ማወቅ የሚገባችሁ መረጃዎች
አሁን በሽታው ያለበት ስርጭት ምን ይመስላል ? በ ሀገራችን እና በ አለም ላይ የተለያዩ አይነት የኮቪድ ዝርያዎች (Variants ) አሉ ? ልዩነታቸው ምንድነው ? በክትባቱ ላይ የሚያመጡት ተፅእኖ ምንድነው? በኮቪድ የተያዘ ሰው ክትባቱን መውሰድ ይችላል ወይ? መቼ ( በምንያህል ጊዜ ውስጥ ?) በ ዓለም ላይ የሚታየው ፍትሓዊ ያልሆነ የክትባት ስርጭት የሚፈጥረው ችግር ምንድነው? እና ከናንተ የደረሱንን ጥያቄዎች መልሰናል ። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2021-04-21
54 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ስለ ቲቢ በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች ! መተላለፊያው ፣ምርመራው ፣ሕክምናው ምን ይመስላል ?
እንደ አለም ጤና ጥበቃ መረጃ በተለምዶ የሳንባ በሽታ የምንለው (ትበርክሎሲስ/ቲቢ ) በ2019 ዓመተ ምህረት በ ዓለም ላይ ከ 1.4 ሚልየን በላይ ሰዎች ሞት ምክንያት ነው። በ ዓለም ላይ ሞትን ከሚያስከትሉ ታላላፊ ተላላፊ በሽታዎች ቁጥር 1 ገዳይ በሽታ ነው ። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከፍተኛ የቲቢ ታማሚ እና በቲቢ ምክንያት ሰዎች ከሚሞቱባቸው 30 አገራት አንዷ ነች። በዚህ ፖድካስታችን ስለ ቲቢ በሽታ እንወያያለን በሽታው ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው እንዴት ይተላለፋል? የበሽታው ዋና ምልክቶች ምንድናቸው? የቲቢ በሽታ በምን አይነት ምርመራ ይረጋገጣል? ሕክምናው ምን ይመስላል ? ሕክምናው ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል? ቤት ውስጥ የታመመ ሰው ካለ ምን አይነት ጥንቃቄ ነው ማድረግ ያለብን ? እነዚህን እና ተያያዥ ጥያቄዎችን እንመልሳለን። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-12-18
50 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
What we know so far about COVID 19 Vaccines? ተገኙ በተባሉት ኮቪድ 19 ክትባቶች ዙሪያ ቆይታ ከዶ/ር በለጠ ጋር
ዶ/ር በለጠ አየለ በ አሜሪካው የጤና ምርምር ተቋም ለረጅም አመት የቫይረሶች ጥናት ተመራማሪ ነበሩ። አሁን ደግሞ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊት ህክምናቸውን ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። በዚህ ፖድካስታችን በቅርቡ ውጤታማ ናቸው የተባሉት የኮቪድ 19 ክትባቶች ዙሪያ መልስ ይሰጡናል። እነዚህ ክትባቶች ምን ያህል ውጤታማ ናቸው ? በፊት ከነበሩ ሌሎች ክትባቶች አንፃር እንዴት ይታያሉ? የክትባቶች መገኘት የበሽታውን ስርጭት ያቆመዋል ወይ? መቼ ከበሽታው መስፋፋት በፊት ወደ ነበረው አኗኗር ልንመለስ እንችላለን? እናንሌሎችንም ጥያቄዎች አንስተን እነጋገራለን ። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-11-28
49 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ጫት በጤናችን ላይ ምን ተፅዕኖ አለው? በኢትዮጲይ እና በአከባቢው ሀገራት የተሰሩ ጥናቶችን እንመለከታለን።
ምን ያህል ሰው ጫት ይጠቀማል? በጫት ውስጥ ያለው ኬሚካል ምንድነው? ሁሉም ጫት አንድ አይነት ነው? በጤናችን ላይ የሚያመጣው ጉዳት ምንድነው? ጫትን ለጥናት የሚጠቀሙ ሰዎች ውጤታማ ናቸው? በእርግዝና ግዜ ጫትን የሚጠቀሙ ሰዎች በፅንሱ ላይ ምን አይነት ጉዳት ያደርሳሉ? በማህበረሰብ ጤና ጫት እንዴት ይታያል? እና ሌሎችንም ነገሮች እንወያያለን ። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-11-03
37 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ትምህርት ቤቶችን መቼ እንክፈት ? የልጆቻችንን፣ የመምህራንን እና የወላጆችን ደህንነት እንዴት እንጠብቃለን? ዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ ይመልሳሉ።
በዚህ ፖድካስታችን የህፃናት ህክምና እና ተላላፊ በሽታዎች ስፔሺያሊስት ሐኪም ዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ ትምህርት ቤቶችን እንዴት የልጆቻንን ደህንነት በጠበቀ መልኩ መክፈት እንደምንችል ፣ ምን አይነት ስጋቶች አሉ? ልጆች ትምህርት ቤት በመቅረታቸው የሚያጡት ነገር ምንድነው? የወላጆችንን ፣የመምህሮቻችንን ጤና እና ደህንነት እንዴት መጠበቅ እንችላለን? እና ሌላም ከአድማጮቻችን የደረሱንን ጥያቄዎች ይመልስልናል። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-10-03
50 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የስትሮክ በሽታ ምንድነው? እንዴት ይታከማል?/እንዴትስ መከላከል ይቻላል?
በዚህ ብፖድካስታችን የምናነሳቸው ነገሮች • ስትሮክ ምንድን ነው? • ለስትሮክ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ምንድናቸዉ? • በስትሮክ የተያዙ ሰዎች ሊያሳያቸዉ የሚችሉ ምልክቶች ምንድናቸዉ? • አንድ ሰው ስትሮክ እንዳለበት እንዴት ማወቅ ይችላል? • አንድ ሰዉ ስትሮክ እንዳለበት እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? • ስትሮክ እንዴት ሊታከም ይችላል? • ስትሮክ ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ይችላል? • ከስትሮክ ቡሃላ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶች ምንድናቸዉ? • የስትሮክ የመልሶ ማቋቋም (Stroke Rehab) • ከስትሮክ በኋላ ሙሉ በሙሉ የማገገም እድሎች በምን ይወሰናሉ? • በሌላ ስትሮክ በድጋሚ ላለመያዝ ምን ማድረግ አለብኝ? --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-09-26
39 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ስለ አስም በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች ?
በዚህ የጤና ወግ ፕሮግራማችን ስለ አስም በሽታ እንንጋገራለን። የአስም በሽታ ምንድነው? ከሌሎች በተለምዶ አለርጂ ፣ ሳይነሳይቲስ ከሚባሉት ህመሞች ያለው ልዩነት ምንድነው? ምልክቶቹ ምንድናቸው? አጣዳፊ ህክምና የሚያስፈልገው መቼን ነው? ዘላቂ ህክምናው ምን ይመስላል? አስምን የሚቀሰቅሱት ነገሮች ምንድናቸው ? እንዴት መከላከል እንችላለን ?/እና ሌሎችንም የመሳሰሉትን ጥያቄዎች አንስተን እንወያያለን ። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-09-11
51 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የደም ማነስ በሽታ ምንድነው ?
በዚህ የጤና ወግ ዝግጅታችን ስለ ደም ማነስ እናወራለን። የደም ማነስ በሽታ የሚከሰተው በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሳት ቁጥር ሲያንስ ወይም በውስጣቸው የሚገኘው ሄሞግሎቢን የሚባለው ሞለኪውል መጠን ሲያንስ ነው። የደም ማነስ በምን ምክንያት ይፈጠራል ? የደም ማነስ ካለብን ምን ምልክቶች እናያለን? በላብራቶሪ የደም ምርምራ የደም ማነስ አለ ምንለው መቼ ነው ? የደም ማነስ እንዴት ይታከማል ? በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ማነስ እና ምክንያቶቹ ፣ የአይረን ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች የትኞቹ ናቸው? እና ስለ ደም መለገስ አንስተን እንወያያለን። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-09-03
25 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ከልክ ያለፈ ውፍረት (Obesity) - ምክንያቶቹ፣ በጤና ላይ የሚያስከትለው ችግሮች እና እንዴት ከልክ ያለፈ ውፍረትን መቀነስ እንደምንችል እንነጋገራለን።
ከልክ ያለፈ ውፍረት (Obesity) ምን ማለት ነው? መቼ ነው ለጤና ጠንቅ መሆን የሚጀምረው ? ውፍረትን በተመለከተ በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ የተዛቡ አመለካከቶች ፣ ከፍተኛ ውፍረትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ምንድናቸው? ውፍረትን ለመቀነስ የሚጠቅሙ ውጤታማ መንገዶች የትኞቹ ናቸው ? --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-08-08
45 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Health Risks of Smoking. ትምባሆ ማጨስ የሚያመጣቸው የጤና እክሎች ምንድናቸው ? እንዴትስ ነው የ ትምባሆ ማጨስን ሱስ መግታት የምንችለው ?
ትምባሆ ማጨስ የሚያመጣቸው የጤና እክሎች ምንድናቸው ? እንዴትስ ነው የ ትምባሆ ማጨስን ሱስ መግታት የምንችለው ? በዚህ ፖድካስታችን ስለ ትምባሆ (ሲጋራ ) ማጨስ ጉዳቶች በሰፊው እንወያያለን ። የ ምናነሳቸው ሃሳቦች 📍 *የትንባሆ አይነቶች ምንድን ናቸው? አጠቃቀማቸውስ? 📍 * አንዱ ከሌላው በሚፈጥሩት ጉዳት ይለያያሉ ወይ? *📍 መደበኛ ሲጋራ ፣ ሺሻ ወይም ሁካ እና የ ኤለክትሮንክ ሲጋራ ያላቸውን ልዩነት እናያለን 📍*ሺሻ /ሁካህ ከ ተለመደው ሲጋራ በባሰ መልኩ እንዴት የጤና ችግር እንደሚያመጣ እንነጋገራለን 📍 *በ እርግዝና ጊዜ የሚያጨሱ ሴቶች ወይም ለሲጋራ ጭስ በተዘዋዋሪ የሚጋለጡ እናቶች በራሳቸው እና በሚወልዱት ልጅ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት አንስተን እንነጋገራለን 📍ከሁለተኛ እጅ የተጎዳኘ ጭስ መጋለጥ የሚፈጥራቸው የጤና ችግሮች ምንድን ናቸው? 📍አጫሾች ማጨስ ቢያቆሙ ምን የጤና ጥቅሞች ሊያገኙ ይችላሉ? 📍ከዚያ በኋላ ሲጋራ ማቆም ጥቅም የለውም የሚባልበት አድሜ አለ አንዴ? 📍ለአጫሾች ለምን ማቆም ይከብዳል? ለማቆም ምን ማረግ አለባቸው? --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-07-15
47 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
በኮቪድ የተያዘ ሰው አራሱን ቤት ውስጥ ማስታመም ቢኖርበት ወይም በኮቪድ የተያዘን ሰው ማስታመም ቢኖርብን ልናውቅ የሚገቡን የጥንቃቄ እርምጃዎች ምንድናቸው?
የኮቪድ በሽታ እየተስፋፋ ከመምጣቱ አንፃር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሁሉንም ታማሚ በጤና ማዕከል መከታተል ላይቻል ይችላል። በኮቪድ የተያዘ ሰው አራሱን ቤት ውስጥ ማስታመም ቢኖርበት ወይም በኮቪድ የተያዘን ሰው ማስታመም ቢኖርብን ልናውቅ የሚገቡን የጥንቃቄ እርምጃዎች ምንድናቸው? በዚህ ፖድካስት 1 በሀገራችን ውስጥ አሁን ያለው የኮቪድ ሁኔታ አንዴት ነው? 2 ከአሜሪካ ተሞክሮ ምን አንማራለን 3 አራሳችንን ቤት ዉስጥ አግለን ስንከባከብ መከተል ያሉብን ነገሮች ምንድን ናቸው? 4 ድንገተኛና አደገኛ ምልክቶቹ ምንድን ናቸው? 5 ቤተሰብ ስንከባከብ መከተል ያለብን ነገሮች ምንድን ናቸው? 6 ቀብርንስ በተመለከተ ምን አዲስ ነገር አለ? ምን አይነት መከላከያዎችን መከተል አለብን? 7 አካል ጉዳተኞች አንዴት የበለጠ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ? ምን ማድረግ ይገባናል? 8 አርጉዝ አናቶችን በተመለከተስ? ጡት ማትባትስ ? ሁሉንም አንስተን ተወያይተናል። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-06-20
51 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ስለ ኩላሊት ህመም ማወቅ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው? ቆይታ ከ ዶ/ር ፍጹም ጥላሁን (የኩላሊት ህክምና ስፔሺያሊስት ) የጤና ወግ አዘጋጅ።
የጤና ወግ አዘጋጆች ዶ/ር ኤርምያስ ካቻ እና ዶ/ር ፍፁም ጥላሁን ስለ ኩላሊት ህመም ተወያይተዋል። የኩላሊት ስራ ምንድነው? አጣዳፊ የኩላሊት ህመም ምንድነው?ዘላቂ የሆነ የኩላሊት ህመም ምንድነው? በምን ምክንያት ይከሰታል? ምልክቶች ምንድናቸው? የኩላሊት ህመም እንዳይባባስ ምን ማድረግ እንችላለን? ኩላሊት አጠቃላይ መስራት ሲያቆም ምን አይነት አማራጭ ህክምናዎች አሉ? የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ከዳያሊስስ የተሻለ አማራጭ ነው የምንለው ለምንድነው? አንድ የኩላሊት ህመም ያለበት ሰው መቼ ነው ዳያሊሲስ ያስፈልገዋል የምንለው?/ --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-06-10
36 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Let's Talk about Suicide. በዚህ የጤና ወጋችን ሰው ለምን ራሱን ወደ መግደል (ራስን ማጥፋት )/ይሄዳል ላይ እንወያያለን።
Yetenaweg Invites Dr.Maji Hailemariam a mental health epidemiologist and assistant professor at Michigan State University and Dr.Azeb Asaminew a Psychiatrist and advisor to Minstry of Health Ethiopia #COVID19 task force on Menatl health and Psycho Social issues to discuss about Suicide. How to discuss about Suicide, who are at risk for suicide, how culture influences how we deal with suicide, what are particular risk posed by COVID19 in incidence of Suicide and how we can particularly help health care professionals in this difficult times. በዚህ ፕሮግራማችን የአእምሮ ጤና ባለሙያዎችን ጋብዘን ስለ አእምሮ ጤና ፣ ራስን ለመግደል ስለሚዳርጉ ምክንያቶች ፣እና ማን የበለጠ ተጋላጭ እንደሆነ እንወያያለን ። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-05-11
53 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Blood donations during #COVID19 በኮቪድ 19 ወቅት ደም ስንለግስ ማወቅ ያለብን ነገሮች።
Regular voluntary blood donations were not habitually seen in Ethiopia in pre-COVID19 times. With travel restrictions and social distancing measures, the Ethiopian blood bank service had faced depleted stores. Dr Brook and Dr Tinsae discuss how blood product shortages can be managed and what precautions to take in the current COVID19 outbreak and outline the huge benefits donors give with their voluntary acts. --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-05-08
28 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
COVID 19 -Current Strategies and Plans Ahead. የ ኮቪድ 19 የፖሊስ አማራጮችና ቀጣይ አርምጃዎች።
We Invited Dr.Tewodros Bekele (MD, MPH) Health Economist who has a rich experience in Health Care Policy and Financing and Dr. Belete Ayele (MD, PhD/Virologist at NIH) to discuss the current #COVID19Ethiopia strategies , what needs to be done in the short and long term to limit the damage from the spread of the disease. Dr. Tewodros brings his experience from other low and Middle income countries on lessons Ethiopia can learn in fighting COVID-19. He set out his 8 steps plan used in other countries. Also discussed why lockdown may not be a good option for Ethiopia , but wo...
2020-04-18
1h 59
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Psychology of Pandemics. በዚህ ወጋችን የአእምሮ ጤናን በወረርሽኝ ወቅት እንዴት እንደምንጠብቅ እንወያያለን።
Yetenaweg invites Dr.MaJi Hailemariam (PhD) who is an assistant professor at Michigan State university and is a mental health epidemiologist to discuss mental health issues in the #coronavirus pandemic, particularly #COVID19Ethiopia. We discuss individual and communal coping mechanisms during Isolation and #SocialDistancing. We also invited Dr.Brook Alemayehu, internist in Ethiopia to share us his experience managing #COVID19 in Ethiopia. We also highlighted, how health care workers are particularly affected and what measures we can take to alleviate the stress they are going through. We also discussed effective communication skills to create trust and avoid unnecessary fear. --- ...
2020-04-15
1h 07
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Care of Chronic diseases in a Pandemic. በ ኮቪድ 19 ምክንያት ከቤት መውጣት ያልቻሉ ሰዎች ህክምና እንዴት ማግኘት ይችላሉ?
እንደ ኮሮና ቫይረስ ያሉ ወረርሽኞች በሚነሱበት ጊዜ ቀጥተኛ ጉዳታቸው ብዙ ነው ። በ ሚድል ኤጅስ ዘመን (Middle Ages ) የተነሳው ጥቁር ሞት (Black Death ) ከ 30-50 ሚልየን ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል። በቅርብ ደግሞ የ HIV pandemic ምክንያት ከ1981 ጀምሮ ከ35 ሚልየን በላይ ሰዎች ሞተዋል። የኮሮና ቫይረስም አሁን በአለም ላይ ከአንድ ሚልየን በላይ ሰዎችን ይዟል። እና ከ 50000 በላይ ሰዎች ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል። የኢኮኖሚ ጉዳቱ ደግሞ በጣም ከፍተኛ ነው። አሁን ማንሳት የፈለግነው ደግሞ በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እንዴት ሌሎች ዘላቂ ህመም ያላቸው ሰዎች በ ክትትል ማነስ ሊጎዱ እንደሚችሉ ነው። በ 2015 የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ሰዎች በ ተላልፊ በሽታው ላለመያዝ ባላቸው ፍራቻ ፣ በ ሆስፒታሎች በአዲስ በሽተኞች መጣበብ ፣ የገንዘብ እና ሌሎች የህክምና ዕቃ መሳሪያዎች ለ ወረርሽኝ መቆጣጠሪያ መዋላቸው የ አነዚህን ህመምተኞች ሕክምና በጣም ይጎዳዋል። ለምሳሌ በ 2014 በ ምዕራብ አፍሪካ የተነሳው የ ኢቦላ ወረርሽኝ ቀጥታ ካመጣው ሞት በተጨማሪ ወደ 11,300 ሰዎች የህክምና ክትትል በማጣት ሞተዋል። በነዚህ ሃገራት ያለው የክትባት ስርጭት መጠን ከ 30% በላይ መቀነሱ ታይቷል። ስለዚህ እነዚህ ተጨማሪ ህመም ያላቸው ሰዎች ሕክምናቸውን የሚያገኙበት መንገድ መመቻቸት አለበት። የተለያዩ የህክምና ተቋማት ይሄንን ክፍተት ለመሙላት ምን እያደረጉ እንደሆነ በዚች አጭር የጤና ወግ ውይይታችን እናያለን ። በ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሌላ ዘላቂ የሆነ የጤና ያለባቸው ሰዎች ሕክምና እንዳይቃረጥ መስራት አለብን --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-04-03
27 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Herd Immunity ምንድነው?
በዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ Herd Immunity ከበሽታ ሊጠብቀን አይችልም። መኖሩንም ማወቅ አንችልም። የተነገሩንን የመከላከል እርምጃዎች እንከተል። Tweet Herd Immunity ማለት በአንድ ማህበረሰብ ያሉ ሰዎች ውስጥ ለ አንድ ተላላፊ በሽታ ምን ያህሉ በሽታውን የመከላከል አቅም አላቸው የሚለውን ነው የሚነግረን። ሰዎች ይሄን የመከላከል አቅም ወይ ታመው ከበሽታው ሲያገግሙ ያገኙታል ወይም በ ሕብረተሰብ ጤና የሚመረጠው ደግም ማህበረሰብ አቀፍ በሆነ የክትባት ዘመቻ ሁልኑም ወይም አብዛኛውን ሕብረተሰብ ማዳረስ ሲቻል ነው። Herd Effect የምንለው ደግሞ በ ማህበረሰብ ውስጥ ከፍ ያለ የ Herd Immunity በመኖሩ የ አንድ በሽታ ከ አንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው የመተላለፍ እድሉ ሲቀንስ ነው። ምን ያህሉ ሰው ለ አንድ በሽታ የመከላከል አቅም ሲኖረው ነው ይሄን Herd Effect የምናየው የሚለው የሚወሰነው በሽታው ምን ያህል ተላላፊ ነው በሚለው ነው። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-04-02
09 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Latest Updates on #COVID19Ethiopia , Dr.Belete (MD,MSc,PhD ) /Virologist answers your questions.
On our Episode today we will discuss #COVID19Ethiopia, Dr. Belete an expert on Viruses at NIH and Dr.Ermias a Pulmonary and Critical care fellow at Cornell will answer your questions about #COVID19Ethiopia. How it is transmitted, Is it Airborne? Who needs to wear masks? What are the common symptoms ? What is the clinical course when you get the virus? What treatment options are available? What are on the pipeline? Any Vaccines? How Clinate affects transmission of the virus in Africa? What human behaviors contribute to emergence of new viruses? How is #COVID19 affecting you individually and how...
2020-03-31
1h 36
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Updates on #COVID19. ስለ አዲሱ ኮሮና ቫይረስ አዳዲስ መረጃዎች እና ማወቅ የሚገባዎት ነገሮች
በዚህ የጤና ወጋችን ስለ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ COVID19 እንወያያለን ። የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ምንድናቸው? ከጉንፋን እና ከኢንፍሉዬንዛ በምን እንለየዋለን ? የተለያዩ በማህበራዊ ሚዲያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተሰራጩ ትክክል ያልሆኑ መረጃዋችን አንድ በአንድ እያነሳን እንወያያለን። የማህበራዊ መራራቅ ስንል ምን ማለታችን ነው ?እንዴት ነው የበሽታውን ስርጭት የሚቀንሰው ? ከእያንዳዳችን ምን ይጠበቃል? እነዚህና ሌሌች ሀሳቦችን አንስተን እንወያያለን። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-03-18
39 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
የሴቶች ጤና ክትትል። በዚህ የሴቶች ጤና ወጋችን በጡት ካንሰር እና በማህፀን በር ካንሰር ላይ እንወያያለን።
የዚህ ክፍል የሴቶች ጤና ውይይታችንን ዶ/ር ኤልሳቤጥ አሳረ እና ዶ/ር ማክዳ ካህሳይ ይመሩታል። ስለጡት ካንሰር እና ማህፀን በር ካንሰር ምልክቶች፣ የትኞቹ ሴቶች ለዚህ ካንሰር የበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ ፣ ምን ምርመራ እና ቅድመ ምርመራ እንደሚይስፈልገን እና ህክምናውስ ምን ይመስላል የሚሉት ርዕሶች ላይ ይወያያሉ። ዶ/ር ኤልሳቤጥ አሳረ በ በኒውዮርክ የሪችመንድ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ሬዚደንት ሀኪም ናት ። እና ዶ/ር ማክዳ ካህሳይ ደግሞ በኒውዮርክ ማውንት ሳይናይ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ሬዚደንት ሀኪም ናት። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-03-18
21 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Sleep Hygiene and what you should know about some Sleep disorders. ስለ እንልፍ ማወቅ የሚገባን ንገሮች ምንድናቸው?
በዚህ የጤና ወጋችን ስለ እንቅልፍ እንወያያለን። በእንቅልፍ ሰአት ሰውነታችን ከመታደሱ በላይ ለሰውነት (በተለይ ለህፃናት) እድገት ቁልፍ የሆኑ ሆርሞኖች የሚመነጩበት ሰአት እንደሆኑ ያውቃሉ? የእንቅልፍ ማጣት እና የእንቅልፍ ማነስ ምንድናቸው? እንዴት ይታከማል? ምን ማድረግ ይገባናል? የእንቅልፍ ማጣት ለደም ግፊት ፣ ለስኳር ህመም ፣ ለሰውነት ከልክ በላይ ውፍረት ለካንሰር ህመም እንደሚያጋልጥ ያውቃሉ ? አልኮል ከመኝታ ሰአት በፊት መውሰድ እንዴት የእንቅልፍ ስረአትን እንደሚያዛባ ለመረዳት እና ሎችንም ጠቃሚ ነጥቦች ለመረዳት ይህን ወግ ያዳምጡ። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-03-02
53 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ስለ ኮሌስትሮል መጨመር ህመም ማወቅ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው? What you need to know about high cholesterol?
የኮሌስትሮል መጠን መጨመር በአለም ላይ የልብ፣ የስትሮክ ፣የደም ዝውውር መቀንስ ህመምን ከሚያመጡ ምክንያቶች ዋነኛው እንደሆነ ያውቃሉ ? በዚህ የጤና ወጋችን የ ኬሌስትሮል መጨመር ህመም ምንድነው? በምን ምክንያት ይከሰታል? የትኞቹ ምግቦች የበለጠ ለ ኮሌስትሮል መጨመር ህመም ያጋልጣሉ? መቼ ነው የ ኮሌስትሮል መጠናችንን መመርመር ያለብን? የኬሌስትሮል መጨመር በምን ይታከማል? የሚሉትን ነጥቦች አንስተን እንወያይለን ።ሌላ ጥያቄ ካላችሁ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገፆቻችን ጥያቄይችሁን ላኩልን ፣ የቻልነውን ያህል በሚቀጥለው ወጋችን ለመመለስ እንሞክራለን ። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-02-16
21 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ስለ አዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው? What you need to know about the new Coronavirus #COVID19 ?
አዲሱ የኮሮና ቫይረስ (በአዲስ የሳይንስ ስሙ COVID-19) ፣ ከየት መጣ ?/ምን ምልክት አለው ?/ በብዛት በህመሙ የሚጠቁት ማናቸው ? በቫይረሱ ሲያዙ ለፀና ህመም ከዛም ባለፈ ለሞት የሚጋለጡት የትኞቹ ህሙማን ናቸው? በሽታው እንዳይዘን ምን ማድረግ አለብን ? በረራ ማቋረጥ የበሽታውን መስፋፋት ይገታዋል? ስለ እነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ይህን የጤና ወጋችንን ተከታተሉን። ሌላ ጥያቄ ካላችሁ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገፆቻችን ጥያቄይችሁን ላኩልን ፣ የቻልነውን ያህል በሚቀጥለው ወጋችን ለመመለስ እንሞክራለን ። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-02-16
29 min
የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
ስለ ደም ግፊት ህመም ማወቅ ያለብን ምንድነው? What you need to know about high blood pressure?
በዚህ የጤና ወጋችን ፣ የደም ግፊት በምን ምክንያት ይከሰታል? የደም ግፊት እንዳለብን በምን እናውቃለን ? የደም ግፊት በቤተሰብ ይተላለፋል ወይ? ደም ግፊታችን ስንለካ ማድረግ ያለብን ጥንቃቄዎች ምንድናቸው? የደም ግፊት በምን ይታከማል? መድሃኒት ባቋርጥ ምን ችግር አለው ?/መድሃኒቱን ለስንት ግዜ መውሰድ አለብኝ ? እና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን እንመልሳለን ። ተጨማሪ ጥያቄ ካላችሁ በፌስ ቡክ እና ትዊተር ገፆቻችን አድርሱን በሚቀጥለው ፕሮግራማችን ላይ የቻልነውን ያህል እንመልሳለን። --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
2020-02-16
50 min